Logo
Explore Menu

Navigation

Preferences

Language / ቋንቋ English
Theological Foundations

የእምነት መግለጫ
Statement of Faith

መጽሐፍ ቅዱስ (The Holy Bible)

ስድሳ ስድቱን የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻህፍት የያዘውን መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር እስትንፋሳ ቃል፣ ምንም ስህተት የማይገኝበት ፣ እምነትን እና ተግባርን በሚመለከት ሁሉ የመጨረሻው ሥልጣን ያለው ፣ህያው እና ዛሬም የሚሰራ ፣ እንደ ሆነ እናምናለን፡፡

02. Holy Trinity

በእግዚአብሔር አብ፣ በእግዚአብሔር ወልድ፣ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፣ አንድ አምላክ ፣እናምናለን፡፡

03. Sovereignty

በመፍጠር ስራ፣ ፍጥረትን በመጠበቅ ፣ በመገለጥ ፣በመዋጀት እና በመጨረሻው ፍርድ የእግዚአብሔርን ፍፁም ሥልጣን እና የበላይነት እናምናለን፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ (Lord Jesus Christ)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብ የተላከ መሆኑን ፣ በመንፈስ ቅዱስ መፀነሱን ፣ ከድንግል ማርያም መወለዱን ፣ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ መሆኑን ፣ ለሰው ልጃች ቤዛ ሆኖ በመስቀል ላይ መሞቱን ፣ መቀበሩን፣ በሶስተኛው ቀን በአካል ከሙታን መነሳቱን፣ ወደ አብ ማረጉን እና አሁንም በአብ ቀኝ ሆኖ ስለ እኛ እንደሚማልድ ፣ ደግሞም በህያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ በክብርና በግርማ እንደሚመለስ እናምናለን፡፡

05. መንፈስ ቅዱስ (Holy Spirit)

መንፈስ ቅዱስ የመለኮት ባሕርያት ሁሉ ያሉት ፍጹም አምላክ እንደሆነ እና አምልኮ እና ስግደት እንድሚገባው እናምናለን፡፡

06. የሰው ልጅ (Humanity)

ሰው በእግዚአብሔር አምሳል መፈጠሩን ፣ በኃጥያት መውደቁን እና በዚህም ምክንያት የእግዚአብሔር ቁጣና ፍርድ ያለበት በደለኛ መሆኑን እናምናለን፡፡

09. መንፈስ ቅዱስ ሙላት (Infilling)

መንፈስ ቅዱስ በአማኝ ህይወት ውስጥ እንደሚኖር ፣ አማኙ በመንፈስ ቅዱስ ሲጠመቅ ኃይልን እንደሚቀበልና በልሳን እንደምናገር በየጊዜውም በመንፈስ ቅዱስ እንደሚሞላ እናምናለን፡፡

07. ድነት (Salvation)

ሰው ከኃጢአት ዕዳ ፣ ኃይልና ቅጣት ፣ ሊድን የሚችለው ኃጥያት የለለበት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ምትክ ሆኖ በፈጸመው የቤዛነት ስራ ብቻ በመሆኑ ኃጥያተኛ በእግዚአብሔር ፀጋ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ብቻ እንደሚጽድቅ እናምናል፡፡

08. ዳግም ልደት (Regeneration)

ኃጥያተኛ በኃጥያቱ ተፀጽቶ ንሰሐ እንዲገባ ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ዳግመኛ በመወለድ አዲስ ፍጥረት እንዲሆን መንፈስ ቅዱስ በህይወቱ እንሚሰራ እናምናልን፡፡

10. የጸጋ ስጦታዎች (Spiritual Gifts)

መንፈስ ቅዱስ ዛሬም ቤተ ክርስቲያንን ለማነጽ ለአማኞች ልዩ ልዩ የጸጋ ስጦታዎችን በማካፈል፣ድውዮችን በመፈወስ ፣ አጋንትን በማውጣትና ፣እና ተዐምራትን በማድረግ እንመድሰራ እናምናለን፡፡

11 & 12. ቤተ ክርስቲያን (The Church & Great Commission)

ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ የተሰጣትን የታላቁን ተልዕኮ አደራ በመወጣት ወንጌልን ለሰዎች ሁሉ እንድትሰብክ እና አማኞች ደቀ መዛሙርት በማድረግ ለክርስቶስ አካል መታነጽ አስፈላጊውን ሁሉ መፈጸም እንደምትችል... በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን፡፡

13. ጥምቀትና የጌታ እራት (Baptism & Communion)

በአብ፣ በወልድ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም በውኃ ውስጥ በመጥለቅ እንዲጠመቅ እንዲሁም ጌታ ዳግም እስኪመጣ ሞቱን ለመናገርና የጌታ እራት እንደሚካፈል እናምናለን፡፡

14. የዘላለም ህይወት (Eternal Life)

በሙታን ትንሳኤ፣ በኃጥያተኞች ላይ በሚደርሰው የዘላለም ፍርድና አማኞች በሚቀበሉት የዘላለም ህይወት እናምናለን፡፡

Soli Deo Gloria

Diyakon Footer Chat On Telegram